ይሄንን ሰሞን አማርኛ አማርኛ ብሎኛል፡፡ ምን አይቼ እንደሆነ አላውቅም፡፡ ትንሽ ልቀላቅል ነው ስለዚህ ታገሱኝ፡፡

በዞሩበት ጠቅላይ ምኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድን ርእስ ካደረገ ጉዳይ ጋር ፊት ለፊት እየተላተሙ ስለሌላ ነገር ማሰብ አልተቻለም፡፡ አሁን እኔም እንደመር ምናምን እያልኩ በአማርኛ ልፅፍ ነው፡፡ ይሄ ሰውዬ ያላመጣው ጉድ የለም፡፡

አይ አም ኤግዚቢት ኤ!

ፓለቲካው፣ ተያያዥ ጉዳዮች፣ ባለፉት ሁለት አመታት የነበረው ጣጣ ቀርቶ ሰውዬው ብቻ ደስ የሚያሰኝ ማይንድ ብሎዊንግ ኤክስፒሪያንስ ነው የሆነብን፡፡ ሰው እንደሆነ ሲያስታውቅበት እንኳን ደካማነት ያልመሰለበት፣ በአፉ ተናግሮ ሊባላ የነበረን ህዝብ እንደዚህ ላስታርቅ እያለ ስለፍቅር፣ይቅርታ ምናምን እያወራ ያፋቀረ ምን አይነት ኤሊያን ነው ይሄ?

ሀቁን እንነጋገርና እነዛ ናሽናሊዝም፣ ፓትሪዮቲዝም ምናምን የሚባሉት ቃላት ፊክሽናል እና አንዳንድ ግዜም ነውር እየመሰሉን እየመጡ ነበረ፡፡ እኔ ራሴ እንደዛ ሳወራላት የነበረችው ኢትዮጲያ ሳንታ ክላውስ ኢዝ ኖት ሪል ሲባሉ እንደሚደነግጡት ልታስደነግጠኝ ነው እያልኩ እንቅልፍ አጥቼ ነበረ፡፡ በሀሳብ ላለመለያየት ዝምታ ሲመረጥ አያየሁ ልፈነዳ ነበረ፡፡ ሰዎች ለካ እንደዛ ያስፈራሉ፡፡

ከዛ ደሞ እንደዛሬውም ይኮናል ለካ? ብወድቅ አያነሳኝም ያልኩት የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ አብይ አይነት ተናጋሪ ብቻ ነበረ ያስፈለገው? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲናገር ራስን በመነቅነቅ ኮንከሽን ስኬር ከማስነሳት ባሻገር አንድ እኔ ያየሁት ነገር እንደሚሰማው ማሳየቱን ነው፡፡ ጆን ግሪን እንዳለው፤ ‹‹ኬሪንግ ኢዝ ሶ አንደርሬትድ›› ጠቅላይ ሚንስትሩ ኬር እንደሚያደርግ አሳይቶ ነው ፍቅር ያስያዘን፡፡

እንደዚህ ቀላል ነበረ?

ፖስት ስክሪፕት፡- ዶክተር አብይ አጎቴ አይደለም፡፡ እንኳን ስለሱ አብረውኝ የሚኖሩትን ሰዎች አውቃቸዋለሁ ብዬ ስለእነሱ መፃፍ ይከብደኛል፡፡ ይሄ ጦማርም አይነቱን ቀይሮ ወቅታዊ ጉዳዮችን ሊተነትን እያሰበም አይደለም ግን ደግሞ ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት አለብን፡፡

1 thought on “እንደዚህ ቀላል ነበረ?

  1. እኔንስ የገረመኝ ይሄው አይደል! ለካ ያ ኪስ ውስጥ እንደዋለ ኢር ፎን የተወሳሰበው የሀገራችን ፓለቲካ አንድ “እንደመር!” የሚል ሰው ነበር የናፈቀው!

Comments are closed.